በምስራቅ ጉራጌ ዞን በክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለወጣቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለወጣቶች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም (ቡታጅራ)

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በ2017/18 በጀት አመት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ከ5000 በላይ ወጣቶች በመሰረታዊ ኮምፒውተር ዕውቀት፣ በኢኮደርስ እና በስፔስ ሳይንስ ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

የመምሪያው ሃላፊ ወ/ሮ ልኬለሽ ከበደ እንደገለጹት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ላይ ተማሪዎች በመሰረታዊ ኮምፒውተር ዕውቀት፣ በኢኮደርስ እና በስፔስ ሳይንስ ስልጠና ተጀምሯል።

ወጣቶቹ በክረምቱ በጎ አድራጎት መርሃ ግብሮች እንደሚሰማሩም አስገንዝበዋል።

ስልጠናው ከሌሎች የክረምት ትምህርት ጋር አቀናጅቶ የሚሠጥ ሲሆን በአግባቡ ጀምረው ለሚያጠናቅቁ ሠልጣኞች በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢንስትቲዩት አማካኝነት ሀገር አቀፍ ሠርተፍኬት የሚሠጥ መሆኑንም ሃላፊዋ ተናግረዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀይሉ ዘውዴ ትምህርቱ ለተማሪዎች የሚሰጠው ከከፍተኛ ተቋም ዩኒቨርሲቲ በመጡ የበጎ ፈቃድ አድራጊ ተማሪዎች ሲሆን፤ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደ ተቋም በይፋ መጀመሩን አስረድተዋል።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብሩ በትኩረትና በትጋት እንዲከናወንም በስፍራው ለተገኙ አካላት አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *